የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎች

የሚኒስትሮች ም/ቤት ታሕሳስ 27 ቀን 2011 ባካሄደው 60ኛ መደበኛ ስብሰባ በአስር የተለያዩ ስምምነቶችና በማጽደቂያ ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡ ም/ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው  በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተዘጋጅተው በቀረቡት የስምምነት ሰነዶች እና የማጽደቂያ ረቂቅ አዋጆች ላይ ሲሆን ስምምነቶቹ፡፡

  • በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በህንድ ሪፐብሊክ የተደረገውን የመረጃ እና የመገናኛ ብዙኃን ስምምነት፣
  • ከኮትድቯር ሪፐብሊክ የዲፕሎማቲክ እና ሰርቪስ ፓስፖርት ለያዙ ሰዎች ቪዛን  ለማስቀረት

የተደረገውን ስምምነት፣

  • ከቬንዙዌላ ቦሊቫሪያ ሪፐብሊክ በባህል ዘርፍ ትብብር ለማድረግ የተደረገውን ስምምነት፣
  • ከጋና ሪፐብሊክ በኮሙኒኬሽን ኢንፎርሜሽን እና በሚዲያ ዘርፍ  የተደረገውን የትብብር ስምምነት፣
  • በሞንተሪያል ፕሮቶኮል ላይ የተደረገውን የኪጋሊ ማሻሻያ ስምምነት፣
  • በስዊስ የፌዴራል ምክር ቤት በመርሃ ግብር የሚከናወን መደበኛ የአየር አገልግሎቶች ስምምነት፣
  • እንዲሁም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል የተደረገውን የዲፕሎማቲክ ፓስፖርት ለያዙ ሰዎች ቪዛን ለማስቀረት የተፈረመውን የመግባቢያ ሰነድ፣ የኢንቨስትመንት ማስፋፊያና ጥበቃ ስምምነት እና የሥራ ስምሪት የመግባቢያ ስምምነት ለም/ቤቱ ቀርበው ውይይት ከተደረገባቸው በኋላ ስምምነቶቹ ለአገራችን የሚያስገኙትን ፋይዳ  ከግምት ውስጥ በማስገባት ም/ቤቱ ረቂቅ አዋጆቹን ተቀብሎ ይጸድቁ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንዲተላለፉ ወስኗል፡፡