የሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔዎች

የሚኒስትሮች ምክር ቤት ህዳር 22 ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

  1. ምክር ቤቱ በቅድሚያ የተወያየው የከተማ ግብርና ልማት ረቂቅ ስትራቴጂ ላይ ሲሆን በከተሞች ከነዋሪዎች ቁጥር መጨመር ጋር ተያይዞ የሚታየውን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ለመፍታት በከተሞች ከሚተገበረው የኢኮኖሚ ዘርፍ መካከል አንዱ የከተማ ግብርና በመሆኑ ዘርፉ ትኩረት ቢሰጠውና በስትራቴጂ ቢታገዝ በከተሞች ለስራ ፈላጊዎች የስራ እድል ለመፍጠር፣ አነስተኛና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን
    የህብረተሰብ ክፍሎች ገቢ ለማሳደግ እና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንዲሁም
    በዘርፉ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች የገበያ ትስስር ከመፍጠርና ጥራቱን የጠበቀ የጥሬ እቃ አቅርቦት ከማመቻቸት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት መሆኑን በመግለጽ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ረቂቅ ስትራቴጂ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ውሳኔ አቅርቧል፡፡ ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ ስትራቴጂ ላይ በዝርዝር ከተወያየ በኋላ ከበልድርሻ አካላት ተጨማሪ ውይይት ተድርጎበት ይበልጥ ዳብሮ እና ተስተካክሎ እንዲመጣ ወስኗል።
  2. ምክር ቤቱ በመቀጠልም የጉምሩክ ኮሚሽንን ተግባር፣ ኃላፊነትና አደረጃጀትን ለመወሰን በተዘጋጀ ረቂቅ ደንብ ላይ የተወያየ ሲሆን ረቂቅ ደንቡ ኮሚሽኑ የህግ ማስከበር፣ የኦፕሬሽንና አገልግሎት የመስጠት ስራዎቹን እንዲያከናውን አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት ምክር ቤቱደንቡን አንዳንድ ማስተካከያዎችን በማድረግ በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል። በመጨረሻ በኢ.ፌ.ዲሪ እና በሩዋንዳ መንግስት መካከል የተደረገውን የመረጃና የመገናኛብዙሃን ስምምነት እና የግብርና ዘርፍ የትብብር ስምምነት፣ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚክኦፖርቹኒቲ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከልየተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ በቀረቡ ረቂቅ አዋጆች ላይ የተወያየ ሲሆንበተለይም ከዓለም አቀፍ የልማት ማህበር በብድር የተገኘው ገንዘብ መንግስት በኢንዱስትሪፓርኮች ልማት እና በስራ ዕድል ፈጠራ ረገድ ያቀዳቸውን ግቦች ለማሳካት እገዛ የሚያደርግሲሆን ብድሩ ከወለድ ነጻ፣ በረጅም ጊዜ የሚከፈልና ከሃገራችን የብድር አስተዳደር ስትራቴጂጋር የሚጣጣም ስለሆነ ተቀብሎ  ስምምነቶቹ ይጸድቁ ዘንድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትእንዲተላለፉ ወስኗል፡፡