የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

Home 100 Days Performance Report


ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡

የተማሪዎች ስብዕና ግንባታ፣ ስነምግባርና ምክንያታዊነትን ማሳደግ

74%

በከፍተኛ ትምህርት ተቋም ውስጥ ጥያቄዎችን በሰላማዊና በአግባብ የማቅረብና ምላሽ የማግኘት፣ እንዲሁም የምክንያታዊነት ባህል እየተፈጠረ ይገኛል

የከፍተኛ ትምህርትና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ጥራትና ተገቢነት

89%

የትምህርትና ሥልጠና ተገቢነት ለማሳደግና የፕሮግራሞች ኦዲት ለማሻሻል ያለው ተቋማዊ አቅም እየጎለበተ ይገኛል

ተቋማትን በልህቀትና ትኩረት መስክ ማደራጀት

100%

ተቋማትን በተልዕኮ ትኩረትና በተዋረድ ለመለየት የሚያስችል ጥናት ተጠናቆ የመለያ መስፈርትና ማስተግበሪያ ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ከአመራር ጋር የጋራ ውይይት እየተደረገ ይገኛል

የሥራ ፈጠራንና የምሩቃንን የመቀጠር እድል የሚያሳድጉ አደረጃጀቶችና ሥርዓት መዘርጋት

71%

ከኢንደስትሪ ጋር በተፈጠረ ትስስርና ትብብር ወደ ንግድ የተቀየሩ ሃሳቦች እየጨመሩ መጥተዋል፤ እንዲሁም ከኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን ጋር ያለ ትስስር እያደገ መጥቷል

የሳይንስና ሳይንሳዊ አሰራሮችን ማጠናከርና መገንባት

56%

የሳይንሳዊ ምርምሮችን ለማከናወን አስፈላጊ የሆኑ የአሰራር ስርዓቶችና የስነ-ምግበር መመሪያ ተዘጋጅቷል

አለም አቀፋዊነትና አጋርነትን ማሳደግ

79%

የትምህርት ተቋማትንና የሴክተሩን አለማቀፋዊነትንና ትብብርን ማሳደግ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ ቀጣይ አቅጣጫዎች
• ተቋማትን በተልዕኮ ትኩረትና በተዋረድ ለመለየት የሚያስችል ጥናት ተጠናቆ የመለያ መስፈርትና ማስተግበሪያ ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ከአመራር የጋራ ውይይት እየተደረገ ይገኛል • በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተግባር ልምምድ ማድረጊያና የሃሳብ ማበልጸጊያ (internship and incubation) ማዕከላት እንዲደራጁ/እንዲጠናከሩ ማድረግ ታቅዶ በ18 የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የተጀመሩ ስራዎች ቢኖሩም አፈጻጸሙ አነስተኛ ነዉ • የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ለልማት ተገቢውን ሚና እንዲጫወት ማስቻል። ለዚህም የተጠና ትስስር ከመንግስትና ከገበያው (ኢንዱስትሪው) ጋር መፍጠር ያስፈልጋል
• በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በጤና ባለሙያዎች እየተነሱ ያሉ የጤና ትምህርት ዘርፍ ካሪኩለም አፈፃፀም ችግሮችን በትኩረት ፈትሾ ከጤና ሚኒስትር ጋር በጋራ መፍታት ቢቻል
• ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ጋር በመተባበር የሀገሪቷን የወደፊት የሰው ሃይል ፍላጎት መተንበይ እና የከፍተኛ ትምህርት ተገቢውን የሰው ሃይል ስብጥርና ቁጥር እንዲያፈራ አድርጎ መቅረጽ
• የሚኒስቴር መ/ቤቱን የሪፎርም ተግባራት ተቋማዊ ቅርጽ መስጠት

የእርስዎ አስተያየት