የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር

Home 100 Days Performance Report


ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡

የአሠሪና ሠራተኛ ጉዳይ ዘርፍ የህግ ተፈፃሚነትን ማረጋገጥ

91%

የአደረጃጀትና አሰራር ማነቆዎች ለመለየት የጥናት ሰነድ ተዘጋጅቷል፤
በ5 የክልል አስተዳደሮችና በ4 የኢንዱስትሪ ፓርኮች ላይ ክትትልና ድጋፍ ተካሂዷል
ለ4 አመት የሚቆይ የ7.6 ሚሊዮን ዶላር ፕሮጀክት ከILO ጋር በጋራ ለመሥራት MOU ተፈርሟል
የኢንሹራንስ ተቋማት በሙያ ደህንነትና ጤንነት አጠባበቅ ዙሪያ አውደ ጥናት ተካሂዷል

የሥራ ገበያ መረጃና የሥራ ስምሪት አገልግሎት ተደራሽነትን ማሳደግ

64%

ለክልል አስፈፃሚዎች የሥራ ስምሪት ባለሙያዎች ወጣቶች በሚያግዙ የሥራ ፍለጋ ክህሎቶች የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጥቷል፣
የሥራ እድሎችን ለመተንበይ የሚያግዝ ዳሰሳ ጥናት በከፊል ተከናውኗል
አሠሪና ሠራተኛ ማገናኛ ኤግዚብሽን ለማመቻቸት ታቅዶ በከፊል ተከናውኗል
በህገ-ወጥ የግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ላይ እርምጃ ተወስዷል

የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት አገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል

75%

ወደ ውጭ ተጉዋዦች ተገቢውን ስልጠናና ክህሎት አግኝተው ወደ ስራ እንዲሰማሩ ለማድረግ የታቀደው በከፊል ተከናውኗል
ከተቀባይ አገራት በሂደት ላይ ያሉ 4 ስምምነቶች በሂደት ላይ ናቸው
ሌበር አታሼ ለመመደብ ቅድመ-ሁኔታዎች ተጠናቋል
3315 ከስደት ተመላሾች (1888 ወንድና 1427 ሴት) ወደ ስራ ገብተዋል
ኢትዮ ማይግራንት ዳታ ቤዝ ተዘጋጅቶ ወደ ሥራ ገብቷል
በአነስተኛ የአገልግሎት ክፍያ ገንዘባቸውን እንዲልኩ የሚያስችል አሰራር በሂደት ላይ ነው

የማህበራዊ ደህንነት አገልግሎትን ተደራሽነት ማሳደግ

77%

ብሄራዊ የማህበራዊ ጥበቃ አገራዊ ኮንፈረንስ ለማካሄድ በታቀደው መሠረት ተካሂዷል
የገቢ ምንጭ የሌላቸው አረጋዊያን ቋሚ የመሰረታዊ አገልግሎት ድጋፍ ለመጀመር መነሻ ረቂቅ የህግ ማዕቀፍ ተዘጋጅቷል
7602 የጐዳና ተዳዳሪዎች ከጐዳና ላይ በማንሳት ተጠቃሚ እንዲሆኑ የልየታ ሥራ ተጠናቋል
ሌሎች አጋሮችን በማስተባበር “ለወደቁት አንሱ” ለተባለው የአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከል የ100 ሺህ ብር ፣ ለሠላም ህፃናት ማሳደጊያ 52 ሺህ ብርና አልባሳት እንዲሁም ለዘውዲቱ ህፃናት ማሳደጊያ 50 ሺህ ብርና የቁሳቁስና አልባሳት ድጋፍ ተደርጓል
በኢትዮጵያ ከሚገኘው ህንድ ኤምባሲ ጋር የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የሰው ሰራሽ አካል ድጋፍ በነፃ የሚያገኙበትን ሁኔታ የመግባቢያ ሠነድ ተፈርሟል

በግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ የማህበራዊ ዋስትና ሽፋን ማሳደግ

88%

ለ3,636 ድርጅቶች የአባልነት ካርድ ለመስጠት ታቅዶ ለ4,594 ተሰጥቷል
1,386 ድርጅቶች በየወቅቱ መዋጮ መክፈላቸውን ለመከታተልና የጡረታ መዋጮ ኦዲት ማድረግ ታቅዶ 1‚210 ድርጅቶችን ኦዲት ማድረግ ተችሏል፡፡
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ ቀጣይ አቅጣጫዎች

• በአሠሪና ሠራተኛ ማህበራት አደረጃጀትና አሰራር ማነቆዎች መለየት የሚያስችል የጥናት ሰነድ ተዘጋጅቷል
• ከ2019-2023 የሚቆይ USD 7,592,055.63 የገንዘብ መጠን የያዘ ፕሮጀክት ከILO ጋር በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈርሟል፡፡ እንዲሁም በኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ የሙያ ደህንነትና ጤንነት ጉዳቶችን በመከላከል ረገድ ከኢንሹራንስ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
• በ4 ኢንዱስትሪ ፓርኮች ሁለት ሜጋ ኘሮጀክቶች ላይ ድጋፋዊ ቁጥጥር በማካሄድ ማስተካከያ ስራዎች እንዲሰሩ ተደርጓል፡፡
• የተለያዩ አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር ለአረጋዊያን እንክብካቤና ህፃናት ማሳደጊያ ተቋማት የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
• በግል ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች አማካይነት ለሥራ የተሰማሩ ዜጎች ላይ እየደረሱ ያሉ የመብት ጥሰቶችን ያደረሱ እና ሕግን ተላልፈው በተገኙ ኤጀንሲዎች ላይ አስፈላጊው ሕጋዊ ዕርምጃዎች ተወስደዋል

• ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ ለመስራት ፍላጎት ያላቸው ዜጎች ተገቢውን ስልጠናና ክህሎት እንዲያገኙ ድጋፍ በማድረግ ወደ ስራ እንዲሰማሩ ማድረግ ላይ በቂ ስራ አልተከናወነም
• የከተማ ልማታዊ ሴፍትኔት ኘሮጀክትን በመጠቀም ውሎና አዳራቸውን በጐዳና ላይ ያደረጉ 7602 የጐዳና ተዳዳሪዎች ከጐዳና ላይ በማንሳት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ላይ በቂ ተግባር አልተከናወነም
• የተለያዩ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በመቋቋም ስኬት ያስመዘገቡ አካል ጉዳተኞችን የህይወት ተሞክሮ በዶክመንተሪ ፊልም በማቅረብ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ

• ወጥ የሆነ አደረጃጀት በክልሎች እስከ ቀበሌ ድረስ እንዲኖር ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረዉ ተግባራዊ ይደረጉ፤
• የስልጠና ተቋማት ብቁና ተወዳዳሪ የሆኑ ሰዎችን አስመርቀዉ ማዉጣት እንዲችሉ የበለጠ ይጠናከሩ፤
• የብሄራዊ ማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲ ተፈፃሚነቱ እንዲረጋገጥ አዳዲስ ፕላትፎም ይዘጋጁ እና ተግበራዊ ይደረጉ፤
• የኢንዱስትሪ ፓርኮች ዉስጥ የሰራተኞችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚሰሩ ስራዎች በይበልጥ ይጠናከሩ፤ የተሰሩ ስራዎች መለኪያ ተቀምጦላቸዉ ተግባራዊ ይደረጉ
• በተለያዩ መስኮች የተማረ የሰዉ ሀይል ወደ ዉጭ መላክና የስራ እድል መፍጠር ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ቢሰራ። ከዚህ ጋር ተያይዞ እንደ ጃፓንና የተባበሩት አረብ ኢምሬት የመሳሰሉ ሀገራት ፍላጎት በማሳየታቸዉ ይህን ጉዳይ ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ተጨባጭ አፈጻጸም ማሳየት

የእርስዎ አስተያየት