የገንዘብ ሚኒስቴር

Home 100 Days Performance Report


ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡

ገቢ መሰብሰብ

86%

የተጨማሪ እሴት እና ተርን-ኦቨር ታክስ የሕግ ማሻሻያ ማዘጋጀት ታቅዶ ረቂቅ የሕግ ሰነድ ለሚ/ሮች ም/ቤት ለማቅረብ ተዘጋጅቷል
የኤክሳይዝ ታክስ ህግ ማሻሻያ ማዘጋጀት ታቅዶ ለጠ/ዓቃቤ ሕግ ተልኳል
ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች ፣ ከመንግሥት ልማት ድርጅቶች ፣ ከባላደራ ቦርድ በድምር ብር 18.521ቢ ታቅዶ በድምር ብር 21.03ቢ ገቢ ተደርጓል
የብድርና የእርዳታ ግኝት ከእቅዱ በላይ ተሳክቷል። በአንጻሩ የብድርና የእርዳታ ፍሰት አፈጻጸም የእቅዱ 74% ነዉ።

የዕዳ ጫናን ማቃለል

63%

የክፍያ ጊዜ እንዲሸጋሸግ ስምምነቶችን በመፈራረም የዕዳ ክፍያ ጫና እንዲቃለል ማድረግ ታቅዶ ከICBC የዋና ገንዘብና የወለድ ክፍያ ቅነሳና የmaturity date ማራዘሚያ፣ ከCET ተከፋይ ሂሳብ ውስጥ 50% ብቻ እንዲከፈል ስምምነትቶች ተደርገዋል

ሀብት ማስተዳደር

88%

ከሀገር ዉስጥ ብድር የሚሸፈን በጀት ጉድለት ከአጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ ከ2.2% እንዳይበልጥ ታቅዶ በዚሁ መሰረት ተግባሮች እየተከናወኑ ናቸዉ
ቅድሚያ ለሚሰጣቸዉ የመንግስት ፕሮጀክቶች በጀት ከፍ እንዲል ተደርጓል (መስኖ ልማት ከ8.5ቢሊዮን ወደ 20 ቢሊዮን)

ሀብት መቆጣጠር፣ የዕዳ ጫናን ማቃለል

81%

በ48 የመንግሥት መ/ቤቶች ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ ከመዝገብ እንዲሰረዝ ታቅዶ 42 መ/ቤቶች ብር 348 ሚሊዮን ተሰርዟል

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሪፎርም

69%

የኮሚኒኬሽን ዘርፍ ሬጉላቶሪ ባለስልጣንን አቋቁሞ ሥራ እንዲጀምር ማድረግ ታቅዶ አዋጁ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በመታየት ላይ ነው
የመንግሥት ልማት ድርጅቶች አዋጅ ከልሶ ለውሣኔ ማቅረብ ታቅዶ በግንቦት ለውሳኔ ለሚኒስትሮች ም/ቤት ይቀርባል
የንግድ ሎጂስቲክስ ፖሊሲ አማራጭ ሰነድ አዘጋጅቶ ለውሣኔ ማቅረብ ታቅዶ የፖሊሲ አማራጭ ሰነድ ለውሣኔ ቀርቧል

አስቻይ ሁኔታዎች

75%

የተቋሙን የሪፎርም ጥናት ለማካሄድ ታቅዶ ጥናቱ ተጠናቆ የዳይሬክቶሬቶች መዋቅር ከሠራተኛው ጋር ውይይት ተደርጎበት ፀድቋል
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ ቀጣይ አቅጣጫዎች
▪ የበጀት ጉድለት ከአጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት ያለው ድርሻ ከ2.2% እንዳይበልጥ ታቅዶ በዚሁ መሰረት ተግባሮች እየተከናወኑ ነው
▪ የህግ ማሻሻያ ስራዎች፣ የድጋፍ ማግኘት እንዲሁም ከተለያዩ ምንጮች የገቢ ማሰባሰብ ስራ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ ነው
▪ የቴሌኮሚኒኬሽን ዘርፍ ሬጉላተሪ ባለስልጣን ማቋቋሚያ አዋጅ ተጠናቋል
▪ የፊስካል ማበረታቻ ታክስ ህግ ማሻሻያ ማዘጋጀት ታቅዶ የመረጃዎች ማሰባሰብ ሥራ ብቻ ተጀምሯል
▪ በራሳቸዉ ዋስትና ብድር የወሰዱ መንግስት ድርጅቶች የዕዳ ክፍያ ሽግሽግ ድርድሮችን ማድረግ ታቅዶ የዝግጅት ስራዎች ብቻ ተከናዉነዋል።
▪ የተቋሙ ዋነኛ ስራ የበጀት ጉድለትን የዋጋ ግሽበት በማያመጣ መልኩ የመቆጣጠር ስራ ስለሆነ ከበሄራዊ ባንክ ብድር ባመዛኙ ከመመርኮዝ ይልቅ በወጪ ቅነሳና በድጋፍ ማሰባሰብ ዙሪያ በተጠናከረ መልኩ ቢሰራ
▪ የመንግስት ልማታዊ ድርጀቶች ሪፎርምን በተመለከተ የሚኒስቴር መ/ቤቱ ሚና በትኩረትና በዝርዝር ቢታይና አካታችነቱ ቢረጋገጥ። የሚቀጥለዉም የ100 ቀን እቅድ የተቋሙን ሚና ግልጽ በሆነ መልኩ የሚያንጽባርቁ ግቦችን ቢያካትት
▪ የተቋሙ በማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር ካለዉ ሚና አኳያ አንጻር የጥናት የምርምርና የሪፎርም አቅሙን ቢያሳድግ
▪ በቀጣይ የእቅድ መርሃግብር ተቋሙ የዉስጥ ሪፎርሙን ቢያጠናቅቅና ምቹ የስራ ሁኔታ መፍጠር ላይ አተኩሮ ቢሰራ

የእርስዎ አስተያየት