የትራንስፖርት ሚኒስቴር

Home 100 Days Performance Report


ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡

የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታና ጥገና

67%

የ840 ኪ.ሜ የመንገድ ግንባታ እና የ4,910 ኪ.ሜ የመንገድ ጥገና ማድረግ ታቅዶ የ452 ኪ.ሜ ግንባታ እና የ2604 ኪ.ሜ መንገድ ላይ ጥገና ማድረግ ተችሏል
የድሬዳዋ ደወሌን አዲስ የክፍያ መንገድ ለአገልግሎት ክፍት ማድረግ ታቅዶ የአፈጻጸም የቅድመ ዝግጀት ስራ እየተሰራ ነው

የባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ

58%

በኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር መስመር የእርማት ስራ አፈጻጸም አሁን ካለበት 80% ወደ 100% በማድረስ ለማጠናቀቅ ታቅዶ የማስተካከያ ከሚያስፈልጋቸው ግኝቶች ውስጥ አንገብጋቢ የሆኑትን የመለየት ስራ ሲሰራ የቆየ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አብዛኛዎቹን ማስተካከል ተችሏል

የመንገድ ትራንስፖርትና የባቡር አገልግሎት

86%

በመናሃሪያዎች የተጓጓዥ የህዝብ ቁጥርን ወደ 25 ሚሊዮን ማሳደግና፤ የቀላል ባቡር በሰሜን - ደቡብ እና በምስራቅ - ምዕራብ አቅጣጫ ጣቢያዎች ላይ የሚደርስበትን ደቂቃ ከ15 ደቂቃ ወደ 12 ደቂቃ ማድረስ ታቅዶ ደቂቃ 12 ወደ ተቀንሷል፣ 25.3 ሚሊዮን ተጓዥ ህዝብ ደርሷል

የአዲስ አበባን ትራንስፖርት አገልግሎት ማሻሻል

69%

በአ.አ ቀላል ባቡር ተጓዥ የነበረውን ምልልስ ወደ 120 ሺ ማድረስና አዳዲስ አውቶብሶች ግዢን 334 ማድረስ ታቅዶ 273 አውቶብሶችና 115,739 ተጓዥ ተደርሷል

የሎጀስቲክስ ውጤታማነት

78%

የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ማዕከል ያደረገ የሎጀስቲክ ወጪን በ5% መቀነስ ታቅዶ በ10% ተቀንሷል
የብትን ጭነት አገባብ 950,000 ቶን ጭነት ታቅዶ 23,000 ቶን ገብቷል

አቪዬሽንን ማሻሻል

80%

ICAO ምዘናን ከ73% ወደ 85% ማድረስ ታቅዶ 80% ማድረስ ተችሏል

የጎለበተ ቅንጅታዊ አሰራር እና ምቹ የስራ አካባቢ

100%

ከተጠሪ ተቋማትና ከክልሎች ጋር አብሮ የማቀድ፣ የመገምገም እና የመደጋገፍ ስርዓትን ማጠናከርና የኤርጎኖሚክስ ስራ ደረጃ በደረጃ ማጠናቀቅ ታቅዶ ተተግብሯል
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ ቀጣይ አቅጣጫዎች
• የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክን ማዕከል ያደረገ ቀልጣፋና ውጤታማ የትራንዚት ትራንስፖርት ስርዓትን ከማረጋገጥ አንጻር የሎጀስቲክ ወጪን በ10 በመቶ መቀነስ ተችሏል
• የአዲስ አበባን ቀላል ባቡር በሰሜን - ደቡብ እና በምስራቅ - ምዕራብ አቅጣጫ ጣቢያዎች ላይ የሚደርስበትን ደቂቃ ከ15 ወደ 12 ደቂቃ ማድረስ ተችሏል
• በሚኒስቴር መ/ቤቱ ምቹ የስራ ሁኔታ ለመፍጠር የተሰሩ የቢሮ ማስዋብ ስራዎች ይበረታታሉ
• የዲሜሬጅ ህግ አፈፃፀምን ከ 89 % ወደ 100% ማድረስ፣ የትራንዚት ምልልስን በ11% መጨመርና የትራንስፖርት ዋጋን በኩንታል 5% መቀነስ ታቅዶ አፈጻጸሙ ዝቅተኛ ነው
• የባቡር መሰረተ ልማት ግንባታ ዙሪያ የታቀዱ በርካታ ግቦች አልተሳኩም
▪ የሎጅስቲክስ ኢንዱስትሪ እንዲስፋፋ ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር በመተባበር አዳዲስ ኢንቨስመንት መሳብና የግል ዘርፉ ተሳታፊት ዙሪያ መስራት
▪በኢትዮ-ጅቡቲ የምድር ባቡር ጭነትን በማሳደግና ሌሎች የማስተካከያ ስራዎችን በመስራት መስመሩ ዉጤታማ እንዲሆን ማስቻል
▪ የሀገሪቷን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ ዙሪያ በበለጠ መልኩ መስራት (ለምሳሌ የሳይክል ትራንስፖርት፣ አዳዲስ መስመሮች መክፈት፣ ተጨማሪ አውቶቢሶች መመደብ፣ የትራፊክ ማኔጅመንት ሲስተምን ማሻሻል፣ ወዘተ)
▪የመንግስት መ/ቤቶችን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ በመንግስት መኪናዎች የuber ሰርቪስ የመስጠት ዙሪያ ጥናት ቢያካሂድ
▪ በዲመረጅ ህግ ዙሪያ የሚታዩትን ችግሮችን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸዉ ተቋማት ጋር በበለጠ በመቀናጀት የተጠናከረ ስራ መስራት

የእርስዎ አስተያየት