ጠቅላይ አቃቤ ህግ

Home 100 Days Performance Report


ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡

የሕግ የበላይነትና የፍትሕ ሥርዓት ግንባታ

83%

ማረፍያ ቤቶች ማሻሻያ ፍኖተ ካርታ፣ የሕግ አስከባሪ አካላት የኃይል አጠቃቀምና የተጠያቂነት ሥርዓትን መዘርጋት ታቅዶ ፍኖተካርታ ተጠናቋል ሆኖም የሥርዓት ዝርጋታው የህግ ማዕቅፍ እየወጣለት ነው
በተደራጁ ቡዱኖች፣ በሰብአዊ መብት ጥሰትና ከባድ የሙስና ወንጀል ክሶች በዕቅድ ጊዜው ውስጥ (100%) ማጠናቅቅ፣ ተጠያቂ እንዲሆኑ መሥራት፣ያልተያዙ ተጠርጣሪዎች በሙሉ እንዲያዙ ማድረግ ታቅዶ 53% ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል
የፀረ ሕገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ግብረሃይል ማስተባበር፣ አደረጃጀቱ ውጤታማ ማድረግ ታቅዶ ፍኖተ ካርታ ዥግጀት ላይ ነው
የፀረ ጥላቻ ንግግር ወንጀል ጥናትና ረቂቅ ሕግ ማጠናቀቅ ታቅዶ የህግ ምዕቀፍ ተዘጋጅቶ ወደ የሚመለከተው አካል ተልኳል

የፍትሕ አገልግሎት አሰጣጥ

79%

የወንጀል መከላከል ስትራቴጂ ማጠቃለልና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ማፀደቅ ታቅዶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲቀርብ ተደርጓል
የንግድ ሕጉን ረቂቅ ክለሳ ሥራ ማጠናቀቅ ታቅዶ በረቂቅ ንግድ ህጉ መጽሃፍት 1፣ 2 እና 5 ላይ ስራ ተጀምሯል
9 በሂደት ላይ ያሉ ሕጎች በማጠቃለል ማስፀደቅ(የፀረ ሽብርተኝነት ረቂቅ፣ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ማሻሻያ አዋጅ፣የምርጫ ሕግ፣የጦር መሳሪያ አያያዝና አስተዳደር አዋጅ፣የመረጃ ነፃነትና የመገናኛ ብዙሃን አዋጅ፣የኃይል አጠቃቀም አዋጅ፣የማረሚያ ቤት ኮሚሽንን እንደገና ለማቋቋም ረቂቅ አዋጅ፣የሕግ ባለሞያዎች አስተዳደር የሕግ፣አስተዳደርና የሕግ ማውጣት ሥነ-ሥርዓትን ማሻሻል) ታቅዶ 44% ተከናውኗል

የሰው ሃብትና ተቋም ግንባታ

80%

የዓቃቢያን ሕግ የሙያ ሥነ ምግባር ደንብ ማፀደቅና መተግበር ታቅዶ ደንቡ ዝግጅት ላይ ይገኛል
ከክልሎች፣ ከተጠሪ ተቋማትና ፖሊስ ቅንጅታዊ አሰራር ዙሪያ በ3 ወሩ የጋራ የግምገማና የልምድ ልውውጥ መድረክ ማካሄድ ታቅዶ በመከናወን ላይ ነው
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ ቀጣይ አቅጣጫዎች

•የፌዴራል ማረሚያና ማረፊያ ቤቶች ማሻሻያ ፍኖተ ካርታን ማጠናቀቅ እና የሃብት ማሰባሰብ ስራ ተሰርቷል
•የፀረ ጥላቻ ንግግር ወንጀል ረቂቅ ሕግ ተጠናቋል
•የሠነዶች ማረጋገጥና ምዝገባ አሰጣጥና መረጃ አያያዝ ሥርዓት ተዘርግቷል

•የንግድ ሕጉን ረቂቅ ክለሳ ሥራ ማጠናቀቅ እቅድ ዙሪያ ድክመት ታይቷል
•በሂደት ላይ ያሉ ሕጎች በማጠቃለል ማፀደቅ እቅድ ዙርያ ጠንክሮ መስራት ያስፈልጋል

•የኢኮኖሚ አሻጥርና የህገ-ወጥ መሳሪያ ዝውውር ዙሪያ በበለጠ ሁኔታ መስራት አለበት
•የማረሚያ ቤት ሪፎርምን ለማሳካት ለታራሚ ስራ ፈጠራ ዙሪያ መሰራት አለበት
•የፀረ ሕገወጥ ንግድና ኮንትሮባንድ ዙሪያ የበለጠ ሚና በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በቀጣይ የ100 ቀን እቅድ ላይ መንጸባረቅ አለበት
•የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የአጭር ጊዜና የረጀም ጊዜ የአቅም ግንባታ እቅድና አፈጻጸም ለወደፊት መንጸባረቅ አለበት። በትኩረት የመርማሪዎች የምርመራ እውቀትና ክህሎት ዙሪያና ዘመናዊ መሳሪያዎች አቅርቦት እና የመሳሰሉት ላይ መስራት። (ለዚህም አጋዥነት በጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በውጭ ሀገራት ያለውን የሰው ሀይል ሞቢላይዝ የማረግ ስራዎች ላይ ያለውን ትልቅ ሚና መጫወት አለበት)
•የፍትህ ስርዓት ማሻሻያ መለኪያ መስፈርት ለማበጀት ከአለም አቅፍ ድርጀቶች ጋር ያለውን አካሄድ ላይ ያተኮረ እቅድ አወጣጥ መተግበር አለበት (ለምሳሌ፡ ከ hague International Law Institute ጋር የጀመረው ስራ)

የእርስዎ አስተያየት