ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር

Home 100 Days Performance Report


ማሰታወሻ፡
+ይህ ግምገማ በሁለተኛው መቶ ቀን ውስጥ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ አፈፃፀም የሚለካ በመሆኑ ሁሉንም የተቋሙን ተግባራት አያካትትም::
+ከዚህ በታች በመቶኛ የተገለፁት ቁጥሮች የብዙ ዝርዝር ተግባራት አማካኝ ውጤቶች ሲሆኑ ከታች የተገለፁት ግን የተመረጡ ዋና ዋና ተግባሮች ናቸው፡፡

አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች የግንባታ ሂደት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ

83%

ለ4 ፓርኮች የሰብስቴሽን ሥራ እንዲከናወን እና ተፈላጊው ግብዓት ማቅረብ ለማስቻል ስራዎች የተጀመሩ ቢሆንም የፖርኮቹን ዝግጁ ከማድረግ አንጻር ብዙ ስራ ይቀራል

የኢንዱስትሪው የማምረት አቅም አጠቃቀም ማሻሻል

75%

10 ሀገር በቀል የቆዳ ፋብሪካዎች የሁለተኛ ደረጃ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያ እንዲያሟሉ ለመደጋፍ ታቅዶ ተከናዉኗል
የሀገር ውስጥ ባለሀብት ከውጭ ሀገር ባለሀብቶች በቅንጅት እንዲሰሩ ለመደገፍ ታቅዶ ተጨባጭ የሆነ ዉጤት ግን አልተገኘም

የዓለም አቀፍና የሁለትዮሽ ንግድ ትስስርን ማጠናከር

75%

የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነት በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለማጸደቅ ታቅዶ ተከናዉኗል

የኤክስፖርት ንግድ አፈፃፀምን ማሳደግ

58%

ከኤክስፖርት ንግድ አፈፃፀምን 1.15 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 690,000 ሚሊዮን ዶላር ተገኝቷል
ሕገወጥ ንግድን ለማሳለጥ የቅንጅት ዕቅድ ሰነድ ለማዘጋጀት ታቅዶ አልተከወነም

የኢንስፔክሽንና ሬጉላሽን ሥራን በማጠናከር ሕገ-ወጥ ንግድን መከላከል

80%

በ488,126 ቶን የገቢ ምርቶች ላይ የጥራት ቁጥጥር ማድረግ ታቅዶ 346,613 ቶን ተከናዉኗል
በ127,500 ቶን የወጪ ምርቶች ላይ ቁጥጥር ማድረግ ታቅዶ 126,498 ቶን ተከናዉኗል

የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎትን ማዘመን

80%

የንግድ ምዝገባ መስፋርቶችን ለማቃለል፣ የአንድ ማእከል አገልግሎት ለመስጠት፣ የካሽ ሬጂስተር ማሽን ማስረከቢያ ጊዜ ለማሳጠር እርምጃዎች ተወስደዋል

ዘመናዊ የግብይት ማዕከላትን ማስፋፋት

93%

የሁመራና በመቱ ማዕከልን አጠናቆ ወደ ስራ ለማስገባት ታቅዶ ተከናዉኗል
የኑግ ምርትን ወደ ዘመናዊ ግብይት ስርዓት ለማስገባት የቅድመ ዝግጅት ስራ የተጠናቀቀ ሲሆን የባቄላን በሚመለከት ተጨማሪ ጥናት በመጠየቁ እየተሰራ ይገኛል

ዋጋ ለማረጋጋትና የስርጭት ፍትሀዊነትን ለማረጋገጥ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ

81%

ዋጋ ለማረጋጋት 110.8 ሚልዮን ሊትር የምግብ ዘይት፣ 1.1 ሚልዮን ኩንታል ስኳርና፣ 1.1 ሚልዮን ኩንታል ስንዴ እንዲቀርብ ተደርገዋል

በአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ የሚታዩ የአሰራር ችግሮችን መቅረፍ

66%

የማምረቻ ማዕከላት ያልተሟሉላቸው መሠረተ ልማት እንዲሟላ ታቅዶ በተለይም በደቡብ ክልል ማከናወን ተችሏል
37,000 የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ 15,561 መፍጠር ተችሏል
ጠንካራ አፈጻጸም ያሳዩ ደካማ አፈጻጸም ያሳዩ ቀጣይ አቅጣጫዎች
▪ በሲስተም/ኤሌክትሮኒክስ አገልግሎት የሚሰጡ የንግድ ምዝገባ ጣቢያዎች ማሳደግ ተችሏል
▪ የአፍሪካ ነጻ ንግድ ቀጣና ስምምነት በሚኒስትሮች ም/ቤት ይሁንታ እንዲያገኝ በማድረግ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ፅድቋል
▪ አዳዲስ ምርቶች ወደ ዘመናዊ የግብይት ስርዓት መግባት፤ የኑግ ምርትን ወደ ዘመናዊ ግብይት ስርዓት ለማስገባት ለቦርዱ ቀርቦ ተቀባይነትን አግኝቷል
▪ የዉጭ ንግድ አፈፃፀም አነስተኛ መሆን፣ ለወጪ ንግድ የፈቃድ አሰጣጥና እድሳት ተጨባጭ ስታንዳርድ ባለመኖሩ ዘርፉ ለህገ ወጥ አሰራሮች ክፉኛ መጋለጥ
▪ ሕገ-ወጥ ንግድን በተመለከተ የቅንጅት ሰነድ እና በወጪ ንግድ የዋጋ መዛባትን/price distortions/ ለከመታተል ጋይድላይን ለማዘጋጀት ታቅዶ አልተጠናቀቀም
▪ በየክልሉ እየተገነቡ ያሉ አግሮ ኢንዱስትሪዎች ከግንባታቸዉ ጎን ለጎን ለኢንዱስትሪዎች የሚያስፈልግ ግብአት በተጠናከር ቅንጅት መስራት ላይ ክፍተት መኖር
▪ ግዴታቸዉን በአግባቡ በማይወጡ (በተለይ default and under invoice የሚያደርጉ) ላኪዎችን በመለየት አስተማሪ እርምጃ መዉሰድ
▪ የሀገር ውስጥ ባለሀብት ከውጭ ሀገር ባለሀብቶች በቅንጅት የሚሰሩበትን አሰራር በተመለከተ በተለይም ለኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚሆኑ ግብአቶችን ማምረትና ማቅረብ የሚችሉበትን ሁኔታ በቅርብ በመከታተልና በመደገፍ ተጨባጭ ዉጤት ማስገኘት
▪ የምርት ገበያን በተመለከተ በርካታ የአሰራር ጉድለቶች የሚታዩ በመሆኑ አሰራር ለማሻሻል ተጭባጭ የሆኑ መለኪያዎች ቢቀመጡና በሚቀጥለዉ እቅድ ቢካተቱ (በተለይም ግልጽና ቀልጣፋ ያሆነ የግብይት፣ የመጋዘንና የግሬዲንግ አሰራር እና ዱካዉን ያረጋገጠ ምርት ማቅረብን (traceability) በተመለከተ)
▪ የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅም አሁንም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ በመሄዱ በዘርፉ ያሉ ገዢ ማነቆዎችን (የግብአት አቅርቦት፣ የሰራተኞች ምርታማነት፣ የፋይናንስ አቅርቦት፣ ወዘተ) መፍታት ላይ በማተኮር ተጨባጭ ስራዎች ቢካተቱ

የእርስዎ አስተያየት